የኢምፔሪያል ተሻጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ለትራፊክ ክፍት ሆነ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።
የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍል እና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ይገኛል።
ውስጠኛው የቀለበት መንገድ ክፍል ላይ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ለመፍታት ተግባራዊ እየተደረጉ ከሚገኙ የመፍትሔ እርምጃዎች አንዱ በዋና ዋና የመስቀለኛ መንገድ መጋጠሚያዎች ላይ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ (overpass) የመገንባት ሥራ ነው።
በዚሁ መሠረት በቦሌ ሚካኤል፣ በኢምፔሪያል እና በለቡ መጋጠሚያ መንገዶች (inter change) ላይ የትራፊክ ማሳለጫ ተሸጋጋሪ ድልድይ (overpass) እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታዎቹን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
ቀደም ሲልም ቦሌ ሚካኤል አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የቀለበት መንገድ ተሸጋጋሪ የትራፊክ ማሳለጫ ድልድይ የግራ ክፍል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መደረጉ ይታወሳል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity