ከቦሌ ሰማይ ስር…
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ከሚገኙ ግዙፍ የመንገድ ማሳለጫ ፕሮጀክቶች መካከል በደቡባዊ ምስራቅ የቀለበት መንገድ ክፍል እየተገነባ የሚገኘው የቦሌ ሚካኤል አደባባይ ተሻጋሪ ድልድይ አንዱ ነው፡፡
ይህ የማሳለጫ ድልድይ 600 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በከተማዋ በግንባታ ላይ ከሚገኙት ትላልቅ የማሳለጫ ድልድዮች በርዝመቱ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል፡፡ የዚህ ማሳለጫ ድልድይ የግራ መስመር ቀደም ሲል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መደረጉም ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ወቅት በቀኝ በኩል ያለውንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል፡፡
ግንባታው ሲጠናቀቅ ቦሌ ሚካኤል አደባባይ ላይ እየተፈጠረ የሚገኘውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር በእጅጉ የሚፈታ ይሆናል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱን አሰር ኮንስትራክሽን እየገነባው ሲሆን የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ ደግሞ ሃይዌይ ኢንጂነርስ አማካሪ ድርጅት እያከናወነው ይገኛል፡፡
የሚሰሩ እጆች የተባረኩ ናቸው!!! መልካም ቀን!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity