ከላፍቶ ድልድይ ወደ ጎፋ መብራት ሀይል የሚወስደው መንገድ በጥገና ላይ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከላፍቶ ወደ ጎፋ መብራት የሚወስደውን መንገድ የጥገና ሥራ ተጀምሯል፡፡ በአካባቢው የነበረዉ የፍሳሽ ቆሻሻ መንገዱን ለብልሽት ከመዳረጉም በላይ ለትራፊክ እንቅስቃሴ መስተጓጎል ዋና መንስኤ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት 400 ሜትር ርዝመት እና 9 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍነውን ነባሩ የአስፋልት ክፍልን ቆርጦ በማንሳት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጥገናዉ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ ከአስፋልት ጥገና ስራው ጎን ለጎን የድሬነጅ መስመር የመልሶ ግንባታ፣ የፅዳት እና ማንሆል ክዳን እድሳት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡የጥገና ስራው የትራፊክ እንቅስቃሴን በማያስተጓጉል መልኩ በእረፍት ቀን እና በሌሊት ክፍለ ጊዜ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity