የኤምፔሪያል ማሳለጫ ድልድይ ሌላኛው የከተማችን ገፅታ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ችግርን ከመፍታት ባሻገር በቀጣይ ለከተማዋ ውብ ገፅታን የሚያጎናፅፉ ትላልቅ የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ ውብ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል ደግሞ የኤምፔሪያል ማሳለጫ ድልድይ ግንባታ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው፡፡ይህ የማሳለጫ ድልድይ ግንባታ ከጫፍና ጫፍ ያሉ መቃረቢያ መንገዶችን ሳይጨምር 300 ሜትር ርዝመትና 40 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡
በአሁኑ ወቅት የድልድዩ የቀኝ መስመር በኮንክሪት ሙሌት ደረጃ ተጠናቆ የትራፊክ አገልግሎት ለመስጠት ከጫፍ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ የግራ መስመሩም ድልድዩ ተገጣጥሞ በመጠናቀቁ የአርማታ ሙሌት ስራ ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ቀሪዎቹ የድልድዩ መቃረቢያ መንገዶች ደግሞ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ፣ የሙሌት እና የሰብ ቤዝ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ የፈጣን አውቶቢስ መስመርም የተካተተበት በመሆኑ በቀጣይ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ከማሻሻሉም ባለፈ ለከተማዋ ውብ ገፅታን የሚያላብስ ይሆናል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity