+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ኮንክሪት ምርት ጭነው በመንገዶች ላይ በሚያንጠባጥቡ ተሽከርካሪዎች ምክንያት መንገዶች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ከጎሮ – ጃክሮሰ የሚወስደው መንገድ ላይ የኮንክሪት ሚክሰር በሚጭኑ ቸልተኛ አሽከርካሪዎች ለአርማታ የተዘጋጀ የሲሚንቶ ኮንክሪት በማንጠባጠብ መንገዱን በተደጋጋሚ ለብልሽት እየዳረጉት ይገኛሉ፡፡

አሁን ላይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መንገዱን የማፅዳት እና የመጠገን ስራ እያከናወነ የሚገኝ ቢሆንም ችግሩ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በህንፃ ግንባታ ወቅት ተሽከርካሪዎች የግንባታ ግብዓቶችንና ተረፈ ምርት ከጭነት በላይ በመጫንና በአግባቡ ባለመሸፈን በአስፋልት መንገዶች ላይ በማንጠባጠብ እንዲሁም ከግንባታ ሳይቶች ሲወጡ ጎማቸውን በአግባቡ ሳያፀዱ ወደ መንገድ በመውጣታቸው በመንገዶች ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ፡፡

በህንፃ ግንባታ ወቅት ከህንፃ ግንባታ ስራ ጋር ተያይዞ ያሉ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል፤ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ረገድ በሚመከለታቸው የደንብ አስከባሪ አካላት የሚወሰዱ የእርምት እርምጃዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ባለስልጣኑ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

ለመንገዶች ብልሽት ምክንያት የሆኑ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል ለታለመለት አላማ እንዲውሉ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡

የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርስን ጉዳት በሚመለከት ጥቆማ ለመስጠት ነጻ የስልክ መስመር 8267 ይጠቀሙ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.