+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በሳምንቱ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የአስፋልት ጥገና ስራ ተከናውኗል

ታህሳስ 15 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአገልግሎት ጫና፣በአጠቃቀም ችግርና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመለየት የጥገና ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የአስፋልት ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከመሳለሚያ- እህል በረንዳ፣ከቦሌ – ሩዋንዳ፣ ከጦር ሀይሎች – ገዳመ እየሱስ፣ ከጦር ሀይሎች – ቶታል አደባባይ፣ከካዛንቺስ ሴቶች አደባባይ – አዋሬ አደባባይ፣ ከኮካ ማዞሪያ – መሳለሚያ እና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የተሳለጠ ለማድረግ የመንገድ ጥገና ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ለመንገዶች ብልሽት ምክንያት የሆኑ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል ለታለመለት አላማ እንዲውሉ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.