በሳምንቱ የተከናወኑ የድሬነጅ መስመር የፅዳት እና የመልሶ ግንባታ ስራዎች በከፊል
ታህሳስ 15 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በክረምት ወቅት በውሃ መፋሰሻ መስመሮች መደፈን ምክንያት የጎርፍ አደጋ ይከሰታል፤መንገዶችም ለብልሽት ይዳረጋሉ በመሆኑም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የድሬኔጅ መስመር መልሶ ግንባታ እና የፅዳት ስራ ከወዲሁ በበጋው እያከናወነ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነዉ ሳምንት የድሬነጅ መስመር መልሶ ግንባታና ፅዳት ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከፒያሳ – አራትኪሎ ፣ ከአቡነጴጥሮስ – ከሊፋ ህንፃ፣ ከአረቂ ፋብሪካ – ባልቻ ሆስፒታል፣ ከመስቀል አደባባይ – ግሎባል ሆቴል፣ ከአራትኪሎ – ግብፅ ኤንባሲ፣አየርጤና ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ፣ከፍየል ቤት- የተባበሩት ፣ሀይሌ ጋርመንት ህዳሴ ት/ቤት አካባቢ እና በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡
የከተማችን ነዋሪዎች እና የድርጅት ባለቤቶች ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመጠቀም የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity