ከእንጦጦ ፍተሻ ኬላ – ፂዮን ሆቴል የተጀመረው የመንገድ መልሶ ግንባታ በአስፋልት ንጣፍ ስራ ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከእንጦጦ የፍተሻ ኬላ እስከ ፂዮን ሆቴል ድረስ ያለውን ነባር መንገድ የመልሶ ግንባታና የጥገና ስራ ማስጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡
መንገዱ ከከተማዋ ወደ ሱልልታ መስመር የመውጫና መግቢያ ኮሊደር በመሆኑ በከባድ ተሸከርካሪዎች ጫና ምክንያት ለጉዳት ተዳርጎ ቆይቷል፡፡
ባለስልጣኑ አሁን ላይ ከእንጦጦ ፍተሻ ኬላ ጀምሮ 1 ኪ.ሜ ገደማ የሚሸፍነውን የመንገዱን የግራ መስመር በመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍና ተያያዥ ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ የቀኝ ክፍል ደግሞ በካፒንግ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሚቀጥሉት አጭር ቀናት ውስጥም የአስፋልት ስራው ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት የሚደረግ ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity