+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች የመፈፀም አቅም የሚያሳድጉ ተከታታይ የሆኑ ስልጠናዎች እየተሰጡ ነው፡፡

ከባለስልጣኑ ከዋናው መስሪያ ቤት የተለያዩ የስራ ክፍሎች፣ ከሎት እና ከመንገድ ሀብት አስተዳዳር ፅ/ቤቶች ለተውጣጡ የአቻ ፎረም ቡድን አባላት በለውጥ አመራር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ላይ በተዘጋጀ ማንዋል ዙሪያ በሶስት ዙር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

የባለስልጣኑ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበዜ ሱሌይማን እንደተናገሩት ስልጠናው የተዘጋጀው በከተማ ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የለውጥ ስራዎችን ለማጠናከር በተዘጋጀ ማኑዋል ዙሪያ ለባለስልጣኑ የአቻ ፎረም ቡድን መሪዎች እና አባላት ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መሰጠቱ ባለስልጣኑ በሚሰጠው የመንገድ መሰረተ ልማት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ወ/ሮ አበዜ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.