+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በሳምንቱ የተከናወኑ የአስፋልት ጥገና ስራዎች በከፊል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ፣10 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት እያከናወናቸው ከሚገኙ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ ነባር መንገዶችን በመለየት እንደ ጉዳት ደረጃቸው የጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ ባሳለፍነው ሳምንት የአስፋልት ጥገና ስራ ካከናወነባቸው የከተማዋ አካባቢዎች መካከል ከለቡ ሙዚቃ ሰፈር- መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን፣ ከአንፎ አደባባይ- አምቦ መንገድ ፣ከቦሌ ቡልቡላ- ሳሪሰ አቦ ፣ሳሪስ ዳማ ሆቴል- ሀና ማሪያም እና ዊንጌት አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ባለስልጣኑ የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ የእረፍት ቀናት ጨምሮ በለሊት ክፍለ ጊዜ የአስፋልት ጥገና ስራዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.