ራስን የማልማትና የመግለፅ ክህሎት ማሳደግ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 5 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ራስን የማልማትና የመግለፅ ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሁለት ቀን ለባለስልጣኑ ሴት ሰራተኞች ሰጠ፡፡
ራዕይን ወደ ተግባር መለወጥ፣የጊዜ አጠቃቀም፣ራስን የመግለፅ እና የማንበብ ክህሎትን እንዴት ማሳደግ ይቻላል? በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች አቅም የሚያሳድጉ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባለስልጣኑ ሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወ/ሪት ፀደንያ አበበ የሴቶችን ክህሎት በማሳደግ ህብረተሰቡ ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀው የስልጠናው ተሳታፊዎች ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ ለሌሎች ሰዎች ማጋራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ያላቸውን ክህሎት ለማሳደግ እና እራሳቸውን ለመለውጥ የሚያስችል ግንዛቤ እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity