+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለስልጣኑ የ5ወራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 3 ቀን 2015ዓ.ም፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራሮች የ5ወራት የመንገድ መሰረተ ልማት የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

የባለስልጣኑ የአምስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድ፣በጀትና እስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ መስፍን ከበረ እንደገለፁት ባለስልጣኑ ባለፉት አምስት ወራት የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም እንደነበራቸው ገልፀው በቀጣይም ቀሪ ስራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ሁሉም የስራ ክፍሎች በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ በበኩላቸው በተሻለ አፈፃፀም የተመዘገቡ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልፀው ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የተቋሙን ውጤታማነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.