+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ሳሪስ አደይ አበባ አካባቢ የድሬነጅ መስመር የመልሶ ግንባታና የፅዳት ስራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 3 ቀን 2015ዓ.ም፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ ምክንያቶች የተዘጉ የድሬነጅ መስመሮች የፅዳትና የመልሶ ግንባታ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በያዝነው ሳምንት የድሬነጅ መስመር መልሶ ግንባታና ፅዳት ስራ እየተከናወነ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች መካከል ሳሪስ አደይ አበባ አንዱ ነው፡፡

በአካባቢው ከመኖሪያ ቤቶች፣ከፋብሪካዎች እና ከሆቴል ቤቶች የሚወጣ የፍሳሽ ቆሻሻ የድሬነጅ መስመር በመዝጋቱ ወደ አስፋልት የሚፈሰው ፍሳሽ መንገዱ ለብልሽት ዳርጎታል፡፡

በተጨማሪምየፍሳሽ ቆሻሻው መጥፎ ሽታ ያለው በመሆኑ ለአካባቢው ነዋሪዎች የጤና ጠንቅ ሆኗል፡፡

ባለስልጣኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት 80 ሜትር ርዝመት ያለው የድሬነጅ መስመር የመልሶ ግንባታ እና የፅዳት ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ የድሬነጅ መስመር መልሶ ግንባታ እና የፅዳት ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ መንገዱን ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ለማድረግ የአስፋልት ጥገና ስራው የሚከናወን ይሆናል፡፡

በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች እና የድርጅት ባለቤቶች ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመጠቀም የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.