17ኛው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም፣– የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች 17ኛውን የብሄር-ብሄረሰቦች ቀን “ህብረ-ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ሀሳብ በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡
እለቱን አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢያሱ ሰሎሞን እንደገለፁት ኢትዮጵያ የተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሀገር መኖሪያ በመሆኗ ከልዩነት ይልቅ አንድነታችንን በማጠናከር የሀገራችንን የሰላም ጉዞ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በትብብር መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የህብረ-ብሔራዊ ስርዓት አተገባበር ጉዟችን የተገኙ መልካም ልምዶች በማስቀጠል ብዙሀነት ያከበረና የተሳሰረ ባህል በመገንባት የተጀመረውን ሁለንተናዊ ሀገራዊ እድገት ማስቀጠል እንደሚገባ አቶ ኢያሱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በጨረሻም በቀረበው የውይይት መነሻ ሰነድ ላይ ተሳታፊዎች ውይይት አካሂደዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
