የፈረንሳይ ፓርክ-ፈረንሳይ አቦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን እያስገነባው የሚገኘው ፈረንሳይ ፓርክ- ፈረንሳይ አቦ የመንገድ ፕሮጀክት በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ሀይል እያስገነባዉ የሚገኘው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 1.2 ኪ.ሜትር ርዝመትና 15 ሜትር የጎን ስፋት አለዉ፡፡
አሁን ላይ 35 ሜትር ርዝመት እና 7.80 ሜትር ከፍታ ያለው የድልድይ ግንባታ ፣ የእግረኛ መንገድ የታይልስ ንጣፍ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 70 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡
የመንገድ ግንባታው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲሆን ከፈረንሳይ ኤንባሲ ወደ ፈረንሳይ አቦ እና ፈረንሳይ ጉራራ አካባቢ መሄድ ለሚፈልጉ አሽከርካሪዎች በአቋራጭነት የሚያገለግል ይሆናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
