የአንፎ የድጋፍ ግንብ ግንባታ 86 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 26 ቀን 2015ዓ.ም፡- ከአለም ባንክ ወደ አንቦ መውጫ መስመር ላይ በተለምዶ አንፎ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የድጋፍ ግንብ ግንባታ 86 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡
በባለስልጣኑ የራስ ሀይል እየተገነባ የሚገኘው ይህ የድጋፍ ግንብ 98 ሜትር ርዝመትና እስከ 10 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን በክረምት ወቅት በአካባቢው የሚከሰት የጎርፍ ስጋትን ለመቅረፍ እና የአስፋልት መንገዱን ከጉዳት ለመጠበቅ ታሳቢ ያደረገ ነዉ ፡፡
አሁን ላይ ከድጋፍ ግንቡ የኮንክሪት ሙሌትና ተያያዥ ስራዎች ጎን ለጎን 110 ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የድሬነጅ መስመር ዝርጋታ የሚከናወን ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
