+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ቀጨኔን ከሽሮ ሜዳ የሚያገናኘው የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ከቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞሪያ እስከ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም ማሪያም ድረስ እየተገነባ የሚገኘውን የመንገድ ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በባለስልጣኑ የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን 1.4 ኪ.ሜ ርዝመት እና 16 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡በአሁኑ ወቅት የመንገድ ፕሮጀክቱ በተሻለ የግንባታ አፈፃፀም ላይ የሚገኝ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ ርዝመት ውስጥ 800 ሜትር የሚሆነው የአስፋልት ንጣፍ የተከናወነለት ሲሆን ቀሪው 600 ሜትር የሚሆነው ደግሞ የአፈር ቆረጣ፣ የድሬኔጅ መስመር ዝርጋታ እና የሙሌት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀጨኔን ከሽሮ ሜዳ ጋር በማገናኘት ለአካባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.