34ኛውን አለም አቀፍ የፀረ-ኤድስ ቀን አስመልክቶ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 23 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ33ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ-ኤድስ ቀን “ፍትሀዊና ተደራሽ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ አገልግሎት” በሚል መሪ ሀሳብ በውይይት እና በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የመግቢያ ንግግረ ያደረጉት የባለስልጣኑ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን ባለሙያ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ተስፋዬ እንደገለፁት በዓለም ዙርያ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ለሚገኝባቸውና በቫይረሱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማሳየት እንዲሁም ህይወታቸውን ያጡትን ለማስታወስ በየዓመቱ እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በማህበረሱ ዘንድ በሽታው ከሀገራችን ጠፍቷል የሚል እሳቤ በመኖሩ ለቫይረሱ የሚሰጠው ጥንቃቄና ትኩረት በመቀነሱ አምራች የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል እያጠቃ እንደሚገኝ ገልፀው ሁሉም ዜጋ እራሱን ከቫይረሱ መጠበቅ እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዕለቱን አስመልክቶ የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ቡድን ሶሻል ወርክ ባለሙያ አቶ አበራ ሶሬሳ በበኩላቸው በሽታው በዓለም ላይ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ ያስከተለ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተቀናጅቶ በመስራት ስርጭቱንና የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንደረዳቸው የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
