+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 68 በመቶ ደርሷል፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ፡- የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀሙ 68 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

በራስ ሀይል እየተገነባ የሚገኘው የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 1 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ8 እስከ15 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡ አሁን ላይ 110 ሜትር ርዝመት ያለው የድጋፍ ግንብ ግንባታ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን የኮብል እና የእግረኛ መንገድ የታይልስ ንጣፍ ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ 800 ሜትር የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት የማልበስ ስራ ተከናውኗል፡፡

ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲሆን በዋናነት ለሰሚት 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎችና ለአካባቢው ህብረተሰብ አገልግሎት በመስጠት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን ይበልጥ እንደሚያጎለብት ይታመናል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.