ሲ.ኤም.ሲ በርታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የድልድይ ግንባታ ስራ እየተከናወ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠታቸው ምክንያት እድሳት የሚያስፈልጋቸውን ድልድዮች ለይቶ ከመጠገን ጎን ለጎን አዳዲስ ድልድዮችን እየገነባ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የድልድይ ግንባታ ሥራ ከሚከናወንባቸው ስፍራዎች መካከል ሲ.ኤም.ሲ በርታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ድልድይ አንዱ ነው፡፡
ድልድዩ 7 ነጥብ 15 ሜትር ርዝመት እና 4 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ ለመኪናም ሆነ ለእግረኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2015 በጀት ዓመት 29 ድልድይ የግንባታና የጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ባለፉት አራት ወራት ብቻ የ7 ድልድዮች ግንባታና የጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
