ከእንጦጦ ፍተሻ ኬላ ወደ ፅዮን ሆቴል አቅጣጫ የሚወስደው ዋና መንገድ አስፋልት ጥገና ተጀምሯል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከእንጦጦ የፍተሻ ኬላ ወደ ፅዮን ሆቴል አቅጣጫ የሚወስደውን ነባር መንገድ በመልሶ ግንባታ ደረጃ የጥገና ስራ ማከናወን ጀምሯል፡፡
በዚህ መስመር ጥገና የሚደረግለት መንገድ ክፍል በአጠቃላይ 3.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1 ኪሎ ሜትር የሚሆነው በመልሶ ግንባታ ደረጃ የሚሰራ ነው፡፡ ቀሪው ደግሞ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆነውን የመንገድ ክፍል ለይቶ በማንሳት ጥገና የሚደረግለት ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት መንገዱ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ሆኖ የጥገና ሥራው ይከናወናል፡፡
ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግደውን ይህን መንገድ በአጭር ጊዜ ጠግኖ ለማጠናቀቅ በትኩረት የሚሰራ ሲሆን፣ የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከሱልልታ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ አሽከርካሪዎች ከእንጦጦ የፍተሸ ጣቢያ ወደ እንጦጦ ማሪያም የሚወስደውን አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአክብሮት ያሳስባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
