ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት አራት ወራት ከ11 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ጠግኗል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አራት ወራት 11.8 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአስፋልት መንገድ ጥገና አከናውኗል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት የአስፋልት ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከአራት ኪሎ – እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን፣ ከዊንጌት – ሳንሱሲ፣ ከአስኮ – አዲሱ ሰፈር ኮንዶሚኒየም እንዲሁም በቦሌ ክፍለ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ መንገዶች ይጠቀሳሉ፡፡
አሁን ላይ ከእንጦጦ ፍተሻ ኬላ ወደ ፅዮን ሆቴል አቅጣጫ የሚወስደው የዋናው አስፋልት መንገድ ጥገና ሥራ ተጀምሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች የከተማዋ ማዕዘናት የመንገድ ጥገና ሥራ ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2015 በጀት ዓመት ከ611 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ለማከናወን አቅዶ እየሰራ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 110 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የአስፈልት መንገድ ጥገና ነው፡፡ ባለፉት 4 ወራት ብቻ ከ287 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን የድሬኔጅና የመንገድ ጥገና እና ሥራዎች ማከናወን ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
