+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣኑ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበር አዳዲስ ስራ አስፈፃሚዎችን መረጠ

አዲስ አበባ፣ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበር ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ የቦርድ አባላት፣ የቁጥጥር እና የብድር ፈቃጅ የስራ አስፈፃሚ አባላትን ምርጫ አካሄደ፡፡

የቀድሞው የማህበሩ ዋና ሰብሳቢ አቶ ታሪኩ ገመቹ የማህበሩን አመታዊ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርበዋል፡፡ ማህበሩ ታህሳስ 1994 በ13 አባላት በ650 ብር ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ 1300 አባላትና 61 ሚሊዮን ብር ካፒታል መድረሱን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ማህበሩ የምግብ ፍጆታና የመገልገያ እቃዎች በብድር ሲያቀርብ መቆየቱን ገልፀው ለትምህርት፣ ለህክምና፣ለኮንዶሚኒየም ክፍያ የብድር አገልግሎት ለአባላቱ መስጠቱን ገልፀዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃ የኦዲት ባለሙያዎች የማህበሩን የ10 ዓመት የኦዲት ሪፖርት ለአባላቱ አቅርበዋል፤ በተጨማሪም አዲሱ የማህበሩ የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ሂደት ተከታትለዋል፡፡

በዚህ መሰረት ሰባት የቦርድ አባላት የተመረጡ ሲሆን ዋና ሰብሳቢ አቶ ባያፈርስ አባተ፣ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ተረፉ ቀፀላ፣ፀሃፊ አቶ ሲሳይ ጎሳዬ፣ ሂሳብ ሹም አቶ ብዙአየሁ ታከለ፣ገንዘብ ያዥ ወይዘሮ አለምሸት ጌታቸው እንዲሁም ሁለት አባላት ተመርጠዋል በተጨማሪ ሶስት የቁጥጥር ኮሚቴ እና ሶስት ብድር ፈቃጅ ኮሚቴ አባላት ተመርጠዋል፡፡

አባላቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃ የቀረበውን የኦዲት ሪፖርትና በቀድሞ የማህበሩ ዋና ሰብሳቢ የቀረበውን ሪፖርት በአብላጫ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን ማህበሩ በአጠቃላይ 73 ሚሊዮን 770 ሺ 817 ብር ከ62 ሳንቲም ቋሚና ተንቀሳቃሽ ሀብት ሲኖረው 2 መቶ ሺ ብር ብድር ለአባላቱ የመስጠት አቅም ላይ ደርሷል፡፡

የቀድሞው የማህበሩ ዋና ሰብሳቢ አቶ ታሪኩ ገመቹ አዲስ ለተመረጡ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ስራቸውን በታማኝነት፣በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.