+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የትራፊክ መጨናነቅ ችግርን ይፈታል ተብሎ የታመነበት የማሳለጫ ድልድይ ግንባታ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ችግርን ይፈታሉ ተብለው በግንባታ ላይ ከሚገኙት ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል የኤምፔሪያል ማሳለጫ ድልድይ አንዱ ነው፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከስርና ከላይ የትራፊክ ፍሰትን ሊያሳልጥ የሚችል 300 ሜትር ርዝምት ያለው የማሳለጫ ድልድይን ጨምሮ አጠቃላይ 1.8 ኪ.ሜ ርዝመትና እስከ 40 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት አለው፡፡

የግንባታ ስራውን ቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ በ800 ሚሊዮን ብር ገደማ በሆነ ወጪ እያከናወነው የሚገኝ ሲሆን፣ ስታዲያ ኢንጂነሪንግ ደግሞ የማማከርና የቁጥጥሩን ስራውን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዋናውን ድልድይ የመገጣጠም ስራ እየተከናወነ ሲሆን አጠቃላይ አፈፃፀሙም ከ58 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ የፈጣን አውቶቢስ መስመርም የተካተተበት በመሆኑ በቀጣይ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ሊሻሽል እንደሚችል ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.