+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የውሃ መፋሰሻ መስመሮች እድሳትና የፅዳት ስራ እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት በአፈር፣ በቆሻሻና መሰል ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ የውሃ መፋሰሻ መስመሮችን በመለየት የፅዳት እና እድሳት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በክረምት ወቅት በውሃ መፋሰሻ መስመሮች መደፈን ምክንያት የጎርፍ አደጋ ይከሰታል፤መንገዶችም ለብልሽት ይዳረጋሉ በመሆኑም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የድሬኔጅ እድሳት እና የፅዳት ስራ ከወዲሁ በበጋው እያከናወነ ይገኛል፡፡

በያዝነው ሳምንት የድሬነጅ የድሳትና የፅዳት ስራዎች ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ሽሮሜዳ፣ መገናኛ፣ ሰሚት እና አያት አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.