+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከቦሌ -ጎሮ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጨማሪ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ -ጎሮ አይ.ሲ .ቲ ፓርክ ድረስ እየተገነባ የሚገኘው የመንገድ ፕሮጀክት ተጨማሪ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ 4.9 ኪ.ሜትር ርዝመትና ከ 30 እስከ 60 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን 1.3 ኪ.ሜ የሚሆነው የመንገዱ ክፍል የእግረኛ መንገዱን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

የዚህን መንገድ ግንባታ አሰር ኮንስትራክሽን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የግንባታ ስራውን እያከናወነው ሲሆን ዩኒኮን አማካሪ ድርጅት ደግሞ የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.