ቂርቆስ ማርገጃ – ቡልጋሪያ የመንገድ ግንባታ በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 5 ቀን 2015ዓ.ም፡- ታህሳስ 10 ቀን 2014ዓ.ም የተጀመረው የቂርቆስ ማርገጃ -ቡልጋርያ የመንገድ ግንባታ በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ሀይል እያስገነባው የሚገኘው ቂርቆስ ማርገጃ- ቡልጋሪያ የመንገድ ፕሮጀክት የመንገዱ አጠቃላይ ርዝመት 1.16 ኪ.ሜትር ርዝመትና የእግረኛ መንገድ ጨምሮ 20 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡
አሁን ላይ 570 ሜትር የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል የመጀመሪያ የአስፋልት ንጣፍ ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀሪው የመንገድ ክፍል ላይ የፓይፕ ቀበራ፣የቦክስ ካልቨርት እና ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ አጠቃላይ አፈፃፀም 52.8 በመቶ ደርሷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግንባታውን በወቅቱ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ የሚገኝ ቢሆንም ቀሪ የወሰን ማስተካከያ ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው በግንባታ ስራው ላይ ተፅኖ አሳድሯል፡፡
ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች መወቅቱ እንዲቀረፉ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የመንገድ ግንባታው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲሆን ከቄራ ወደ ለገሃር እና ቂርቆስ ቤተክርስትያን አካባቢ መሄድ ለሚፈልጉ አሽከርካሪዎች በአቋራጭነት በማገልገል በአካባቢው ላይ ያለውን የትራፊክ ጫና የሚያቃልል ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
