+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአንበሳ ጋራዥ – ናሳው ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ ፣ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራስ ኃይል እያስገነባቸው ከሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የአንበሳ ጋራዥ – ናሳው ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 1.2 ኪ.ሜ ርዝመት እና የእግረኛና የሳይክል መስመርን ጨምሮ 30 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል እየተገነባ የሚገኘው ይህ የመንገድ ፕሮጄክት አሁን ላይ የመንገዱ የግራ መስመር የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ማልበስ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ በመንገዱን የቀኝ መስመር ላይም የሰብ ቤዝ፣ የቤዝ ኮርስ፣ የከርቭ ስቶን እና የቦክስ ከልቨርት ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ አጠቃላይ አፈፃፀሙም 65.5 በመቶ ደርሷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ የመንገድ ፕሮጀክቱን እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የግንባታ ስራውን አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ቢገኝም፣ የተወሰኑ የመብራት ምሰስዎች እና የግለሰብ አጥሮች ከመንገድ ፕሮጀክቱ የወሰን ክልል ውስጥ ባለመነሳታቸው የግንባታ ስራው በተፈለገ ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅእኖ አሳድረዋል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የወሰን ማስከበር ስራዎቹን በማጠናቀቅ የዘወትር ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ባለስልጣኑ መልክቱን ያስተላልፋል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ከጀሞ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በአርሴማ ቤተክርስቲያን በኩል ወደ ለቡ መብራት ለማቋረጥ አማራጭ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.