+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታቸው ቆሞ የነበረው የሁለት መንገዶች ግንባታ ሥራ ቀጥሏል

ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ አደባባይ የሚወስደው የመንገድ ፕሮጄክት ግንባታ 74 በመቶ ደርሷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ከወሰን ማስከበር እና ከፋይናንስ ጋር በተያያዙ አበይት ችግሮች ምክንያት ግንባታቸው ቆሞ የነበረው የቃሊቲ – ቱሉ ዲምቱ አደባባይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እና ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ አደባባይ የሚወስደው የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀምሯል።

የቃሊቲ -ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት የቀኙ መስመር የመጀመሪያ ደረጃ የአስፋልት ንጣፍ ስራ እና የሦስት ማሳለጫ ድልድዮች የስትራክቸር ስራ ተከናውኖ መንገዱ በከፊል ለትራፊክ ክፍት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ አጋጥሞት በነበረው የፋይናንስ እና የወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት የግንባታ ስራው ተቋርጦ ቆይቷል።

አሁን ላይ ከፋይናንስ ጋር በተያያዘ አጋጥሞ የነበረው ችግር የቻይና ኤግዚም ባንክ ብድር እስከሚለቀቅ ድረስ ከመንግስት በጀት በብድር መልክ ክፍያ እየተፈፀመ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባስተላለፈው ውሳኔ የተፈታ በመሆኑ የመንገዱ የግራ መስመር የግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በመንገድ ፕሮጀክቱ የግራ መስመር ላይ ገብርኤል ቤተክርስቲያን፣ ኬኬ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና ጋሪ ድልድይ አካባቢ ላይ የአፈር ቆረጣ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ 56 በመቶ የደረሰ ሲሆን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የመንገዱን የግራ ክፍል የመጀመሪያ ደረጃ አስፋልት በማልበስ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በቻይና ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን 11 ኪ.ሜ ርዝመትና 50 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ግንባታው ቆሞ የነበረው የቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ – ቡልቡላ – ቂሊንጦ አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀምሯል።

በአሁኑ ወቅት የድልድይ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፣ በዚህ በጀት ዓመት ቀሪ የግንባታ ስራዎችን በማጠናቀቅ መንገዱን ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 10.5 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5.6 ኪ.ሜ የሚሆነው አስፋልትለብሷል። የግንባታ ስራውን ቻይና ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ካምፓኒ እያከናወነው ሲሆን የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ስራውን ደግሞ ሀይ ዌይ ኢንጂነርስ ኮንሰልታንት እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህ የመንድ ፕሮጀክት 10.5 ኪ.ሜ ርዝመትና 40/50 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.