በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ ጥገና ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ምክንያቶች አልፎ አልፎ ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን በመለየት እንደ ብልሽት መጠናቸው የጥገና ስራዎችን በተሻለ ሁኔታ እያከናወነ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት የጥገና ስራዎች ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካካል ከቃሊቲ ማሰልጠኛ – ሀና ማሪያም፣ከአየር ጤና ትራፊክ መብራት – ጦርሀይሎች፣ ከጦር ሀይሎች-18 ማዞሪያ፣ ከደጃች ውቤ – ፒያሳ፣ ከፒያሳ- ሰሜን ማዘጋጃ የሚወስደው መንገድ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የአስፋልት ጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity