በበጀት ዓመቱ 90 ኪ.ሜ የኮብል መንገዶችን ለመገንባት በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት 90 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ መንገዶች ለመገንባት አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት 3 ወራት 11.2 ኪ.ሜ የሚሆን የኮብል መንገዶችን የገነባ ሲሆን በዚህም 634 በማህበር የተደራጁ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአስፋልት መንገዶች ግንባታና ጥገና ጎን ለጎን የከተማዋን የመንገድ ሽፋን ለማሳደግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማህበር የተደራጁ ወጣቶችን በማሳተፍ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት የኮብል መንገዶች የግንባታ ስራውን አጠናክሮ የሚያስቀጥል ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity