ተቋማት በሚያስገነቧቸው ግንባታዎች ምክንያት በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በተለምዶ አፍንጮ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ ባለው የአጥር ግንባታ ምክንያት ሙሉ በሙሉ በአፈርና የግንባታ ተረፈ ምርት የእግረኛ መንገዱ እና በከፊል የአስፋልት መንገዱ በመዘጋቱ የትራፊክ እንቅስቃሴ እየተስተጓጎለ ይገኛል፡፡
የሰሜን አዲስ አባባ የመንገድ ሀብት አስተዳደር የሳይት ኢንጅነር በላይ ለማ እንደገለፁት ባለስልጣን መስርያ ቤቱ የግንባታ ተረፈ ምርቱ እንዲነሳ በተደጋጋሚ ለዩኒቨርሲቲው ቢያሳውቅም ምንም አይነት ምላሽ ሊገኝ ባለመቻሉ የእግረኞችን እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ እና በመንገድ ሀብቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በዚህም ምክንያት እግረኞች በመኪና መንገድ ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የመንገድ ዳር የውሃ ፍሳሽ መስመሮች ላይ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት እንደሚያስከትል ኢንጅነር በላይ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው በፍጥነት የማስተካከያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ኢንጅነር በላይ አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity