የድሬነጅ መስመሮች ጥገና እና ግንባታ ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 25 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቆሻሻና በተለያዩ ምክንያቶች የተደፈኑ የውሃ መፋሰሻ መስመሮችን እየጠገነ ይገኛል፡፡
በያዝነው ሳምንት የድሬነጅ ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ሲቪል ሰርቪስ ሂልሳድ ት/ቤት፣ ኮልፌ ወረዳ 6፣ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም፣ ጉርድ ሾላና መሳለሚያ አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በያዝነው በጀት ዓመት ከ341 ኪሎ ሜትር በለይ ርቀት የሚሸፍን የድሬነጅ መስመር ፅዳትና የጥገና ስራዎች ለማከናውን አቅዶ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ ከ1.8 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬነጅ መስመር የጥገና እና የግንባታ ስራዎች አከናውኗል።
የመንገድ ዳር የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው ዓለማ እንዲወሉ በማድረግ በኩል የከተማችን ነዋሪዎች ድርሻ እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ህብረተሰቡ የመንገድ ሀብቱን በአግባቡ እንዲጠቀም ባለስልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
