የድሬኔጅ መስመሮች የተሰሩት ለንጹህ የዝናብ ውሃ መፋሰሻ ብቻ ነው
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመዲናዋ የድሬኔጅ መስመሮች በተገቢው መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በየጊዜው የድሬኔጅ መስመር ጥገናና ፅዳት ስራ ያከናውናል፡፡
በተለይም በክረምት ወቅት ለሚከሰተው የጎርፍ አደጋ የውሃ መፋሰሻ መስመሮቻችን በቆሻሻ መደፈን ዋነኛው ምክንያት በመሆኑ በበጋው ወራት የሚከናወነው የፅዳትና የጥገና ስራ ወሳኝ ነው፡፡
ነገር ግን በክረምት ወራት እየገጠመ ላለው የመንገዶች በጎርፍ መጥለቅለቅ መፍትሄ ያለው በነዋሪዎች እጅ ጭምር ነው፡፡ የከተማው ነዋሪ እና ድርጅቶች ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ ከቻሉ የውሃ ማስወገጃ መስመሮች ተገቢውን አገልግት መስጠት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም የፍሳሽ ቆሻሻን ከውሃ ማስወገጃ መስመሮች ጋር ከማገናኘት መቆጠብ ሌላው መፍትሄ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍሳሽ መስመሮችና የውሃ መውረጃ ቱቦዎች የተሰሩበት አላማም ሆነ አገልግሎታቸው የተለያየ በመሆኑ፡፡
ስለሆነም የድሬኔጅ መስመሮቻችን ከቆሻሻ ማጠራቀሚያነት ነፃ ሁነው በተገቢው መልኩ ለተሰሩበት አላማ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ሁላችንም የበኩላችንን ሃላፊነት በመወጣት ፅዱና ውብ ከተማን እንፍጠር!
ማንኛውንም ከመንገድ ሃብት ጋር የተገናኘ ጥቆማ ለመስጠት በ ነጻ የስልክ መስመር 8267 ይደውሉ
ፎቶ፡- አሁን ላይ ከአፍሪካ ህብረት እስከ ልደታ ፀበል የድሬኔጅ መስመር ፅዳት ስራ ሲከናወን
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
