+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የለቡ ማሳለጫ ድልድይ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በስራ ተቋራጮች እያስገነባቸዉ ከሚገኙት በርካታ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነዉ የለቡ መብራት ኃይል ማሳለጫ ድልድይ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ድልድዩን ሊሸከሙ የሚችሉ ምሰስዎች /pillars/ ግንባታ የሙሌት ስራ ተገባዶ ዋናውን ድልድይ የማስቀመጥ ስራ ተጀምሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የማንሆል ግንባታ፣ የዩቲሊቲ መስመሮች ዝርጋታ፣ የድጋፍ ግንብ እና የመቃረቢያ መንገዶች የገረጋንቲ አፈር ሙሌት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡ አጠቃላይ አፈፃፀሙም 40 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራው በስታዲያ ኢንጂነሪንግ ስራዎችአማካሪ ድርጅት በኩል እየተሰራ ይገኛል፡፡

የማሳለጫ ድልድየ አጠቃላይ 2.3 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ20 – 46 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ግንባታውን እስከ 20 ወራት ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዟል፡፡

የማሳለጫ ግንባታው ሲጠናቀቅ አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ከመፍታቱም ባሻገር ለከተማዋ የገፅታ ግንባታ መሻሻል አዎንታዊ ሚናው የጎላ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.