+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ እየተሳሉ የሚገኙ የመንገድ ዳር ሥዕሎች ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን እያጎናፅፉ ነው

አዲስ አበባ፣ 21 ቀን 2015 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያውያን የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች ከተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር በመተባበር ወዳጅነት፣ ሠላምና ተስፋን የሚያንፀርቁ የስነ-ጥበብ ሥራዎችን በመስራት ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ውበት በማጎናፀፍ ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ እና የብራዚል ሰዓሊያን በጋራ በመሆን በብራዚል ኤምባሲ የገንዘብ ድጋፍ ፑሽኪን አደባባይ የታችኛው መተላለፊያ መንገድ ግድግዳ ላይ የሰሯቸው ሁለት ስዕሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ የብራዚል ኤምባሲ ተወካይ፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አስፋው ዲንጋሞ እንዲሁም የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሞገስ ጥበቡ ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከመንገድ መስረተ-ልማት ማስፋፋት ዋነኛ ተልዕኮው በተጨማሪ ለጎዳና ላይ ስዕል ሥራ የሚመቹ መንገዶችን ለይቶ ፍቃድ በመስጠት እና ደረጃቸውን የጠበቁ ስዕሎች እንዲሳሉ በመከታተል ለከተማዋ መልካም ገፅታ ግንባታ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የብራዚል ሰዓሊዎች በጋራ በመጣመር የሰሯቸው ስዕሎች ከተማዋን የሚያስውቡ ከመሆናቸውም ባሻገር በሀገራቱ መካከል የስነ-ጥበብ እና የባህል ልምድ ልውውጥ እንዲዳብር እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም በቀጣይ ባለስልጣኑ የከተማዋን መልካም ገፅታ የሚጨምሩ የመንገድ ዳር ስዕሎች ለማሰራት በዕቅድ ይዞ እየሰራ የሚገኝ በመሆኑ የሙያው ባለቤት የሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ ሰዓሊያን እና ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማት የከተማዋን ጎዳናዎች በስዕል የማስዋብ ስራ ላይ እንዲሰተፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.