በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የግንባታ ግብዓቶች ማምረት ተችሏል
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ባላለፉት 3 ወራት ብቻ ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ ግብዓቶች አምርቷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ እያመረታቸው የሚገኙ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ምርቶች በራስ አቅም ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች መፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡
በሩብ ዓመቱ ከተመረቱት የግንባታ ግብዓቶች መካከል 20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የካባ ምርቶች፣ 16 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የሲሚንቶ ውጤቶች እና 3 ሚሊዮን ብር በላይየሚያወጡ የአስፋልት ኮንክሪት ውጤቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity