+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 297 የመንገድ ወሰን ማስከበር ስራዎች ተሰርተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በመንገድ ግንባታ ሥራ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ያለውን የወሰን ማስከበር ችግር ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተካሄደ ቅንጅታዊ ሥራ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 3 ወራት 297 የመንገድ ወሰን ማስከበር ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በመንገድ ግንባታ ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኙ 130 ቤቶች፣ 140 የመብራት እና 27 የቴሌ ምሰሶዎችን ከሚመለከታቸው የክፍለ ከተማና የወረዳ አስተዳደር አካላት ጋር ቅንጅት ማስነሳት ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ ሥራዎች ስኬት በአጠቃላይ 4 ሺህ 535 ልዩ ልዩ ግንባታዎች እና የመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎችን ከመንገድ ወሰን ክልል ውስጥ ለማስነሳት አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡

በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እና በቅርቡ ውል የተገባላቸውን አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሥራ ማስጀመር ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በላቀ ቅንጅታዊ አሰራር የወሰን ማስከበር ሥራዎችን ከወዲሁ በማጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.