+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከጎሮ አደባባይ- አይሲቲ ፓርክ የሚወስደው መንገድ የጥገና ስራው 250 ሜትር ርዝመት በ15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ሲሆን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የጥገና ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከጎሮ አደባባይ – አይሲቲ ፓርክ የሚወስደው መንገድ የጥገና ስራ እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት የመንገድ ጥገና ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በክረምት ወቅት በሚከሰት ጎርፍና በተለያዩ ምክንያች ብልሽት የገጠማቸውን መንገዶች በመለየት የጥገና ስራዎችን በማከናወን የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በያዝነው ሳምንት የጥገና ስራዎች እየተከናወነ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች መካከል ከጎሮ አደባባይ- አይሲቲ ፓርክ የሚወስደው መንገድ ተጠቃሽ ነው፡፡

የጥገና ስራው 250 ሜትር ርዝመት በ15 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ሲሆን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የጥገና ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በአካባቢው በአብዛኛው ከባድ መኪኖች የሚንቀሳቀሱበት እና ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ ከተሞች የመውጫ መንገድ በመሆኑ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት አካባቢ በመሆኑ የጥገና ስራው መከናወኑ በአካባቢው የነበረውን የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከአፍንጮ በር- ደጃች ውቤ እንዲሁም ከአለም ባንክ- አንፎ አደባባይ የሚወሰደው መንገድ የጥገና ስራ በያዝነው ሳምንት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.