+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በመንገድ ሀብት ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን መከላከል የሚያስችል የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመንገድ ሀብት ላይ ህገወጥ ተግባራት በሚፈፅሙ ተቋማት እና ግለሰቦች ላይ የእርምት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ደምበል ጌቱ ኮሜርሻል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአስፋልትና በእግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ ግብዓት በማስቀመጥ መንገድ የዘጉ ግለሰቦች እንዲያነሱ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸው ያስቀመጡት የግንባታ ቁሳቁስ በግብረ ኃይል እንዲነሳ መደረጉን የባለስልጣን መስሪያቤቱ የማዕከላዊ አዲስ አበባ መንገድ ሀብት አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የግንባታ ግብዓቱ 16 ሜትር ኪዩብ አሸዋ፣ 8 ሜትር ኪዩብ ጠጠር እና 370 ብሎኬት በአጠቃላይ 56,850 ብር ግምት ያለው ሲሆን፣ አሁን ላይ በግንባታ ግብዓቶች ተዘግቶ የነበረው የአስፋልትና እግረኛ መንገድ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በቀጣይም በመንገድ ሀብት ላይ የሚፈፀመውን ህገወጥ ተግባር ለመከላከል የእርምት እርምጃዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል መንገዶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በትኩረት ይሰራል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.