አንፎ አካባቢ የድጋፍ ግንብ እየተገነባ ይገኛል
አዲስ አበባ ጥቅምት 18 ቀን 2015 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአለም ባንክ ወደ አምቦ መውጫ መስመር ላይ በሚገኘውና በተለምዶ አንፎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 90 ሜትር ርዝመትና እስከ 10 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ያለው የድጋፍ ግንብ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡
የድጋፍ ግንቡ ግንባታ በአካባቢው የጎርፍ ስጋት በመኖሩ የአስፋልት መንገዱን ከጉዳት ለመጠበቅ ያለመ ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የጎርፍ አደጋ ስጋቱን ለመቀነስ የሚያስችል የድሬኔጅ መስመር ግንባታም የሚከናወን ይሆናል፡፡
በአሁኑ ወቅት የድጋፍ ግንቡ የኮንክሪት ሙሌትና ተያያዥ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን አጠቃላይ አፈፃፀሙም ከ45 በመቶ በላይ መድረስ ችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity