አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አመራሮች በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሳይንስ ሙዚየም የጉብኝት መርሀ ግብር አካሄዱ፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አመራሮች በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እውን ሆኖ ሳይንስና ቴክኖሎጂን በጉልህ በማሳየት ሀገራዊ ዕድገትን ለማፋጠን ያግዛል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የሳይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ባዩት የፈጠራ ውጤቶች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በሙዚየሙ የቀረቡት የሳይንስና የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች በቀጣይ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለምትሰራቸው በርካታ ስራዎች ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጠር ገልፀዋል፡፡
አዲስ በተገነባው የሳይንስ ሙዚየም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር የሳይንስና ቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ለእይታ ክፍት ያደረጉ ሲሆን ወደፊት የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂና የሳይንስ እድገትን በማጠናከር ተስፋ የሚጣልባቸው መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
በተጨማሪም የባለስልጣኑ አመራሮች ለእይታ ውብና ሳቢ የሆነውን የወዳጅነት ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንደዚህ አይነት የጉብኝት መርሀ ግብር ማዘጋጀቱ የሰራተኞችን የስራ ተነሳሽነት በመጨመር የመፈፀም አቅምን ለማሳደግ አስተዋፆ ያበረክታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity