+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ የአስፋልት መንገዶችን በመለየት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ የአስፋልት ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ገርጂ መብራት ኃይል፣ ኃይሌ ጋርመንት አደባባይ፣ ብሔራዊ ትያትር፣ ዓለም ባንክ፣ ከአራት ኪሎ ፒያሳ- ሲኒማ አምፔር፣ ከጎሮ አደባባይ – ሰሚት ለስላሳ መጠጥ ፋብሪካ፣ ጎፋ ካምፕ፣ ከጀሞ ሚካኤል – አንበሳ ጋራጅ እና ሌሎች አካባቢዎችም ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በያዝነው በጀት ዓመት 611.7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ የጥገና ስራዎችን ለማከናወን በእቅድ የያዘ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ሩብ ዓመትም ከ214 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆን የተለያዩ የመንገድ የጥገና ስራዎች አከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.