+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለስልጣኑ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 235.83 ኪሎ ሜትር የግንባታና የጥገና ስራዎችን አከናወነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 261.18 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የግንባታና የጥገና ስራዎች ለመስራት አቅዶ 235.83 ኪ.ሜ በማከናወን የእቅዱን 90 በመቶ ለማሳካት ችሏል፡፡

በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑት የግንባታ ስራዎች መካከል 1.85 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 4.25 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 1.54 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ 11.2 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ፣ 3.46 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ መልሶ ግንባታ፣ 0.04 ኪ.ሜ የዲሬኔጅ መስመሮች እና 0.4 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ስራዎችን የሚያካትት ሲሆን በድምሩም 21.05 ከ.ሜ ይሸፍናሉ፡፡

በተመሳሳይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 4.25 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 8.29 ከ.ሜ የጠጠር፣ 186.93 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ፅዳት፣ 1.8 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመሮች እድሳትና ጥገና፣1.55 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራ፣1.44 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ መከለያ አጥር ጥገና እንዲሁም 10.38 ኪ.ሜ የመንገድ ቀለም ቅብ ስራዎች በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ አብይ ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ላይ በክረምቱ ከባድ ዝናብና በስርቆት ምክንያት አገልግሎት ያቋረጡ 3 ሺ 40 የመንገድ ዳር የመብራት አምፖሎችን በአዲስ መልክ በመቀየር ሰላማዊ የምሽት እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.