የድሬነጅ መስመሮች ጥገና ስራ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተጋለጡ የድሬነጅ መስመሮችን በመለየት የፅዳትና የጥገና፣ እንዲሁም ክፍት የሆኑ የውሃ መፋሰሻ መስመሮችን የመክደን ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የውሃ መፋሰሻ መስመሮች ፅዳትና የጥገና ስራዎች እያከናወነ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች መካከል ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 5፣ አስኮ አዲስ ሰፈር፣ 5ኪሎ ናዝሬት ትምህርት ቤት አካባቢ እና አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መሰል የድሬነጅ ጥገና ስራዎች በማከናወን በክረምት ወቅት የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመከላከል ተከታታይ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ማከናውኑን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የመንገድ ሀብት ተጠቃሚ የሆነው መላው የከተማችን ነዋሪም ለመንገድ መሠረተ-ልማቱ ደህንነት መጠበቅ የበኩሉን ገንቢ ሚና እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity