+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከአየር ጤና – አለም ባንክ ወደ አንፎ አደባባይ የሚወስደው መንገድ በጥገና ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ጥገና ስራዎችን አጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ የተለያዩ አከባቢዎች በክረምት ወቅት በሚከሰት ጎርፍ እንዲሁም ረጅም ዓመታት አገልግሎት በመስጠት በመንገዶች ላይ በሚከሰት ጉዳት የትራፊክ እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉሉ መንገዶችን በመለየት የአስፋልት የጥገና ስራዎችን በትኩረት እያከናወነ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የአስፋልት የጥገና ስራዎች እየተከናወነ ከሚገኙባቸው አካባቢዎች መካከል ከአየር ጤና- አለም ባንክ አንፎ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ይገኝበታል፡፡

የጥገና ስራው 3.9 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት እየተጠገነ ይገኛል፡፡

አካባቢው በአብዛኛው ከባድ መኪኖች የሚንቀሳቀሱበት በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ የነበረበት ሲሆን የአስፋልት የጥገና ስራው መከናወኑ ቀደም ሲል በአካባቢው የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ የትራፊክ እንቅስቃሴው የተሳለጠና ምቹ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.