ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ወደ 72 የሚወስድ መንገድ ተጠግኖ ለትራፊክ ክፍት ሆነ
አዲስ አበባ፣ጥቅምት 4 ቀን 2015ዓ.ም፤- የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት የአስፋልት መንገዶች ጥገና ስራ በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡
አሁን ላይ የመንገድ ጥገና እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ወደ 72 ማዞርያ የሚወስደው መንገድ ይገኝበታል፡፡
የጥገና ስራው 134 ሜትር ርዝመት በ7 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ሲሆን የተጎዳውን የአስፋልት ክፍል ቆርጦ በማንሳት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተጠግኖ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል፡፡
የአስፋልት የጥገና ስራው መከናወኑ ቀደም ሲል በአካባቢው የነበረውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ የትራፊክ እንቅስቃሴው የተሳለጠና ምቹ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity