+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የኬላ ፈረንሳይ- ፈረንሳይ አቦ ቤተ ክርስትያን አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፡- ጥቅምት 4 ቀን 2015 ፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የኬላ ፈረንሳይ- ፈረንሳይ አቦ ቤተ ክርስትያን የአስፋልት መንገድ የፕሮጀክት በተያዘው በጀት ዓመት ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ በትኩረት እተሰራ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ 1.2 ኪ.ሜትር ርዝመት በ15 ሜትር የጎን ስፋት እየተገነባ የሚገኝ አቋራጭ መንገድ ነው፡፡ አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ርዝመት ውስጥ 700 ሜትር የሚሆነው የአስፋልት ማልበስ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን የእግረኛ መንገድ፣ የየድጋፍ ግንብ፣ የድልድይ እና ተያያዥ ቀሪ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡ አሁን ላይ አጠቃላይ አፈፃፀሙም 62 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

የመንገዱ ግንባታ ስራ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት በሚሆንበት ወቅት በዋናነት ለፈረንሳይ ፓርክ እንደ አማራጭ መንገድ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከፈረንሳይ ኬላ ወደ ፈረንሰይ ጉራራ ኪዳነ ምህረት እና አካባቢው መሄድ ለሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ ሆኖ የሚያገለግል ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው ያለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ይበልጥ በማሳደግ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.