+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2015 በጀት ዓመት ለማከናወን ያቀዳቸውን ዋና ዋና ግቦች መሰረት በማድረግ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በበጀት ዓመቱ ለሚያከናውናቸው የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ይረዳ ዘንድ በመሠረተ ልማት ዝርጋታና አቅርቦት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ከሚሰሩ የከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ ተቋማት ጋር በ2015 በጀት ዓመት ለማከናወን ያቀዷቸውን ዋና ዋና ተግባራት መሰረት በማድረግ የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም የበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ በሆነው የመጀመርያው ሩብ ዓመት ተቋማቱ ያከናወኗቸውን ዝርዝር ተግባራት የሚገልፅ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በየተቋማቱ ኃላፊዎች ቀርቦ በጋራ ተገምግሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.