+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የሰሚት 40/60 ኮንዶሚንየም የአስፋልት መንገድ ግንባታ 70 በመቶ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ፡- የሰሚት 40/60 ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ 70 በመቶ ተጠናቋል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በግንቦት ወር መጨረሻ 2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን 1 ኪ.ሜትር ርዝመትና ከ8-15 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡ 800 ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል አስፋልት የለበሰ ሲሆን ቀሪው 200 ሜትሩ ደግሞ በወሰን ማስከበር ምክንያት መጠናቀቅ አልተቻለም፡፡ አሁን ላይ የእግረኛ መንገዱ የሰብ ቤዝ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለታይልስ ለንጣፍ ዝግጁ ሆኖ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የድጋፍ ግንብ እና ተያያዥ የውስጥ ለውስጥ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡ አሁን ላይ አጠቃላይ አፈፃፀሙም 70 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራ በማጠናቀቅ በኩል የድርሻቸውን እንዲወጡ ባለስልጣኑ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የመንገድ ግንባታው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሲሆን በዋናነት ለሰሚት 40/60 የጋራ መኖርያ ቤት ነዋሪዎች አገልግሎት ከመስጠቱ በተጨማሪ የአከባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.